It was ordered that individuals who were in prison for more than 3 years be released from prison.

 It was ordered that individuals who were in prison for more than 3 years be released from prison.




The 1st Corruption Cases Criminal Court of the Federal High Court has ordered the release of individuals who have been in prison for more than 3 years, including the case file of the former director of the Security Bureau.




The new accused, Samuel Gidisana, has been ordered to be released from prison yesterday for serving more than the sentence decided by the court.


በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ከተከሰሱት በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ተካተው የነበሩት 17ኛ ተከሳሽ አዲሱ በዳሳ 18ኛ ሳሙኤል ጊዲሳ እና 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነው ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።


እነዚሁ ሦስቱ ተከሳሾች በየካቲት 25 ቀን 2014 በነበረ የችሎት ቀጠሮ "ባልሰራንበት ወንጀል አራት ዓመት ታስረናል፤ የተፋጠነ ፍትህ ለማግኘት እንድንችል የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ አንፈልግም።" በማለት ጉዳያቸው ተነጥሎ ፍርድ እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበረም ይታወሳል።


በተለይም 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነው ያለጥፋቱ አራት ዓመት መታሰሩን ጠቅሶ በእያንዳንዷ ቀናት ቤተሰቦቹ ከቀለብ ጀምሮ መቸገራቸውን ገልጾ ነበር።ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ፍርድ ይፍረድብን እና እንረፍ ሲሉ የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙ እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል።


በዚሁ የካቲት 25 ቀን 17ኛና 18ኛ ተከሳሽ የነበሩት አዲሱና ሳሙኤል የቅጣት ማቅለያ አስተያየት አያይዘው በጽሁፍ አቅርበው ነበር።


ፍርድ ቤቱም ከክስ መዝገቡን የሦስቱን ተከሳሾች ጉዳይ ነጥሎ መርምሯል።


በዚህም ተከሳሾቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውና ለአገር ልማት ያደረጉትን አስተዋጾ አክለው ያቀረቡትን 5 የቅጣት ማቅለያ ፍርድ ቤቱ ይዞላቸዋል።


በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ትላንት ከሰዓት በኋላ በዋለው የችሎት ቀጠሮ፤ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ በተባሉበት አንቀጽ አዱሱ በዳሳና ሳሙኤል ጊዲሳን እያንዳንዳቸውን የ3 ዓመት እስራትና የ3 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፤ 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነውን በተመለከተ ደግሞ በኹለት ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።


በዚህም መሰረት አዲሱ በዳሳና ደርሶ አየነው ከታሰሩበት ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ ታሳቢ ሲደረግ፤ ከቅጣቱ በላይ በመታሰራቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከትላንት ጀምሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መሰጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።


ሳሙኤል ጊዲሳን በተመለከተም እስካሁን የታሰረበት ጊዜ በመዝገቡ ላይ ያልተካተተ ቢሆንም፤ የታሰረበት የጊዜ መጠን ተጣርቶ በተመሳሳይ ከእስር የሚፈታ ይሆናል ተብሏል።

Post a Comment

0 Comments